1. እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ማንን እፈራለሁ?
2. ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።
3. ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ልቤ አይፈራም፤ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ልበ ሙሉ ነኝ።
4. እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤እርሷንም እሻለሁ፤ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።
5. በመከራ ቀን፣በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤
6. በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤እዘምርለታለሁም።
7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ራራልኝ፤ ስማኝም።
8. “ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ልቤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።
9. ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤መቼም ረዳቴ ነህና።አዳኝ አምላኬ ሆይ፤አትጣለኝ፤ አትተወኝም።