1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣አንተው ፍረድልኝ።ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።
2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤መርምረኝም፤ልቤንና ውስጤን መርምር፤
3. ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣በእውነትህም ተመላለስሁ።
4. ከማይረቡ ጋር አልተቀመጥሁም፤ከግብዞችም ጋር አልተባበርሁም።
5. የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ከዐመፀኞችም ጋር አልቀመጥም።
6. እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህንም እዞራለሁ፤