መዝሙር 25:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ዐይኖቼ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።

16. እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።

17. የልቤ መከራ በዝቶአል፤ከጭንቀቴ ገላግለኝ።

18. ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።

19. ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።

20. ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።

21. አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።

22. አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን፣ከመከራው ሁሉ አድነው።

መዝሙር 25