መዝሙር 21:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. የልቡን መሻት ሰጠኸው፤የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም። ሴላ

3. መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት።

4. ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።

5. ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።

መዝሙር 21