መዝሙር 20:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።

2. ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።

3. ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ። ሴላ

4. የልብህን መሻት ይስጥህ፤ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።

መዝሙር 20