መዝሙር 2:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።

7. የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤

8. ለምነኝ፤መንግሥታትን ርስት አድርጌ፣የምድርንም ዳርቻ ግዛት እንዲሆንህ እሰጥሃለሁ።

9. አንተም በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፤እንደ ሸክላ ዕቃ ታደቃቸዋለህ።”

10. ስለዚህ እናንት ነገሥታት ልብ በሉ፤እናንት የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ።

መዝሙር 2