መዝሙር 2:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ፣ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤

3. “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ።

4. በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ጌታም ይሣለቅባቸዋል።

5. ከዚያም በቊጣው ይናገራቸዋል፤በመዓቱም ያስደነግጣቸዋል፤

6. ደግሞም፣ “እኔ ግን በተቀደሰው ተራራዬ፣በጽዮን ላይ የራሴን ንጉሥ ሾምሁ” ይላል።

7. የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤

መዝሙር 2