መዝሙር 2:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሕዝቦች ለምን ያሤራሉ?ሰዎችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ?

2. የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ፣ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤

3. “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ።

4. በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ጌታም ይሣለቅባቸዋል።

መዝሙር 2