መዝሙር 18:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቍር ደመና ነበረ።

10. በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።

11. ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤በዝናብ አዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።

12. በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ፣ደመናት፣ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ ወጡ።

መዝሙር 18