መዝሙር 147:6-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።

7. ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

8. ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።

9. ለእንስሳት ምግባቸውን፣የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።

10. እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።

11. ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።

12. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽን አወድሺ፤

13. እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአል።

መዝሙር 147