መዝሙር 146:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ።ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።

2. በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርንአመሰግናለሁ፤በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ።

3. በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ።

4. መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።

5. ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤

መዝሙር 146