መዝሙር 144:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣የተሞሉ ይሁኑ፤በጎቻችን እስከ ሺህ ይውለዱ፤በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ።

14. ከብቶቻችን ይክበዱ፤አይጨንግፉ፤ አይጥፉም።እኛም በምርኮ አንወሰድ፤በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ።

15. ይህ ባርኮት ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው።

መዝሙር 144