መዝሙር 139:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ መረመርኸኝ፤ደግሞም ዐወቅኸኝ።

2. አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ።

3. መሄድ መተኛቴን አጥርተህ ታውቃለህ፤መንገዶቼንም ሁሉ ተረድተሃቸዋል።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ፣እነሆ፤ አንተ ሁሉንም ታውቃለህ።

መዝሙር 139