መዝሙር 136:8-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ፀሓይ በቀን እንዲሠለጥን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

9. ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲሠለጥኑ ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

10. የግብፅን በኵር የመታ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

11. እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

12. በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

13. የኤርትራን ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

መዝሙር 136