መዝሙር 136:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

13. የኤርትራን ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

14. እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

15. ፈርዖንንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ያሰጠመ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

16. ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

መዝሙር 136