1. እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2. የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3. የጌቶችን ጌታ አመሰግኑ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
4. እርሱ ብቻውን ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
5. ሰማያትን በብልኀት የሠራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
6. ምድርን በውሃ ላይ የዘረጋ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
7. ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤