መዝሙር 135:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. በእግዚአብሔር ቤት፣በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት።

3. እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤

4. እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና።

5. እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነ፣ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና።

6. በሰማይና በምድር፣በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ሁሉ ያደርጋል።

7. እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤መብረቅ ከዝናብ ጋር እንዲወርድ ያደርጋል፤ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል።

8. በኵር ሆኖ በግብፅ የተወለደውን፣ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ቀሠፈ።

መዝሙር 135