መዝሙር 132:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “ወደ ማደሪያው እንግባ፤እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።

9. ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”

10. ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው አትተወው።

11. እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።

መዝሙር 132