መዝሙር 132:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ዳዊትን፣የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ፤

2. እርሱ ለእግዚአብሔር ማለ፤ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤

3. “ወደ ቤቴ አልገባም፤ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤

4. ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤

5. ለእግዚአብሔር ስፍራን፣ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”

6. እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤በቂርያትይዓሪም አገኘነው።

መዝሙር 132