መዝሙር 13:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ስማኝም፤የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤

4. በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ።

5. እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።

6. ቸርነቱ በዝቶልኛልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።

መዝሙር 13