መዝሙር 121:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?

2. ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።

3. እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤የሚጠብቅህም አይተኛም።

4. እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ፣ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።

5. እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።

6. ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አታመጣብህም።

መዝሙር 121