መዝሙር 119:71-75 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

71. ሥርዐትህን እማር ዘንድ፣በመከራ ውስጥ ማለፌ መልካም ሆነልኝ።

72. ከአእላፋት ብርና ወርቅ ይልቅ፣ከአፍህ የሚወጣው ሕግ ይሻለኛል።

73. እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ትእዛዛትህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ።

74. ቃልህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይበላቸው።

75. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍርድህ የጽድቅ ፍርድ፣ያስጨነቅኸኝም በታማኝነት እንደሆነ ዐወቅሁ።

መዝሙር 119