መዝሙር 119:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የጽድቅ ፍርድህን ስማር፣በቅን ልብ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።

8. ሥርዐትህን እጠብቃለሁ፤ፈጽመህ አትተወኝ።

9. ጒልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል?በቃልህ መሠረት በመኖር ነው።

10. በሙሉ ልቤ ፈለግሁህ፤ከትእዛዛትህ ፈቀቅ እንዳልል አድርገኝ።

11. አንተን እንዳልበድል፣ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ቡሩክ ነህ፤ሥርዐትህን አስተምረኝ።

13. ከአንደበትህ የሚወጣውን ደንብ ሁሉ፣በከንፈሬ እናገራለሁ።

መዝሙር 119