መዝሙር 119:55-59 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

55. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን በሌሊት ዐስባለሁ፤ሕግህንም እጠብቃለሁ።

56. ሥርዐትህን እከተላለሁ፤ይህችም ተግባሬ ሆነች።

57. እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ቃልህን ለመታዘዝ ቈርጫለሁ።

58. በፍጹም ልቤ ፊትህን ፈለግሁ፤እንደ ቃልህ ቸርነትህን አሳየኝ።

59. መንገዴን ቃኘሁ፤አካሄዴንም ወደ ምስክርህ አቀናሁ።

መዝሙር 119