መዝሙር 119:36-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

36. ከራስ ጥቅም ይልቅ፣ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል።

37. ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ።

38. ትፈራ ዘንድ፣ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ፈጽም።

39. የምፈራውን መዋረድ ከእኔ አርቅ፤ደንብህ መልካም ነውና።

40. እነሆ፤ ድንጋጌህን ናፈቅሁ፤በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።

መዝሙር 119