መዝሙር 119:30-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. የእውነትን መንገድ መርጫለሁ፤ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ።

31. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከምስክርነትህ ጋር ተጣብቄአለሁ፤አሳልፈህ ለውርደት አትስጠኝ።

32. ልቤን አስፍተህልኛልና፣በትእዛዛትህ መንገድ እሮጣለሁ።

33. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ፤እኔም እስከ መጨረሻው እጠብቀዋለሁ።

34. ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው፣ ማስተዋልን ስጠኝ።

መዝሙር 119