መዝሙር 119:25-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ነፍሴ ከዐፈር ተጣበቀች፤እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።

26. ስለ መንገዴ ገልጬ ነገርሁህ፤ አንተም መለስህልኝ፤ሥርዐትህን አስተምረኝ።

27. የድንጋጌህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፤እኔም ድንቅ ሥራህን አሰላስላለሁ።

28. ነፍሴ በሐዘን ተዝለፈለፈች፤እንደ ቃልህ አበርታኝ።

መዝሙር 119