መዝሙር 119:162-168 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

162. ትልቅ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፤በቃልህ ደስ አለኝ።

163. ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ፤ሕግህን ግን ወደድሁ።

164. ጻድቅ ስለ ሆነው ሕግህ፤በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ።

165. ሕግህን የሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ዕንቅፋትም የለባቸውም።

166. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ትእዛዝህንም እፈጽማለሁ።

167. ነፍሴ ምስክርነትህን ትጠብቃለች፤እጅግ እወደዋለሁና።

168. መንገዴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነውና፣ሕግህንና ምስክርነትህን እጠብቃለሁ።

መዝሙር 119