መዝሙር 119:125-131 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

125. እኔ ባሪያህ ነኝ፤ምስክርነትህን ዐውቅ ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

126. እግዚአብሔር ሆይ፤ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው።

127. ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ትእዛዛትህን ወደድሁ።

128. መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

129. ምስክርነትህ ሁሉ ድንቅ ነው፤ስለዚህ ነፍሴ ትጠብቀዋለች።

130. የቃልህ ትርጓሜ ያበራል፤አላዋቂዎችንም አስተዋዮች ያደርጋል።

131. ትእዛዝህን ናፍቄአለሁና፣አፌን ከፈትሁ፤ አለከለክሁም።

መዝሙር 119