መዝሙር 119:122-128 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

122. ለባሪያህ በጎነት ዋስትና ሁን፤እብሪተኛ እንዲጨቍነኝ አትፍቀድላቸው።

123. ዐይኖቼ ማዳንህን፣የጽድቅ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ።

124. ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ መጠን አድርግ፤ሥርዐትህንም አስተምረኝ።

125. እኔ ባሪያህ ነኝ፤ምስክርነትህን ዐውቅ ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ።

126. እግዚአብሔር ሆይ፤ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው።

127. ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ትእዛዛትህን ወደድሁ።

128. መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

መዝሙር 119