መዝሙር 119:105-108 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

105. ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ለመንገዴም ብርሃን ነው።

106. የጽድቅ ሕግህን ለመጠበቅ፤ምያለሁ፤ ይህንኑ አጸናለሁ።

107. እጅግ ተቸግሬአለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ።

108. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈቅጄ ያቀረብሁትን የአፌን የምስጋና መሥዋዕት ተቀበል፤ሕግህንም አስተምረኝ።

መዝሙር 119