መዝሙር 118:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

7. ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

8. ሰውን መከታ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

9. በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

10. ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

መዝሙር 118