መዝሙር 118:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የአሮን ቤት፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

4. እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣“ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበሉ።

5. በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።

6. እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

7. ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

መዝሙር 118