መዝሙር 115:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አሕዛብ፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?

3. አምላካችንስ በሰማይ ነው፤እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።

4. የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ የሠራቸው፣ብርና ወርቅ ናቸው።

5. አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣

6. ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤

7. እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤በጒሮሮአቸውም ድምፅ አይፈጥሩም።

8. እነዚህን የሚያበጁ፣የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።

መዝሙር 115