1. ለእኛ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለእኛ ሳይሆን፣ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህ፣ለስምህ ክብርን ስጥ።
2. አሕዛብ፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?
3. አምላካችንስ በሰማይ ነው፤እርሱ ደስ የሚለውን ያደርጋል።
4. የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ የሠራቸው፣ብርና ወርቅ ናቸው።
5. አፍ አላቸው፤ አይናገሩም፤ዐይን አላቸው፤ አያዩም፣
6. ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤አፍንጫ አላቸው፤ አያሸቱም፤