መዝሙር 113:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?

7. ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤

8. ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።

9. መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።ሃሌ ሉያ።

መዝሙር 113