መዝሙር 112:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ክፉ ወሬ አያሸብረውም፤ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው።

8. ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።

9. በልግስና ለድኾች ሰጠ፤ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል፤ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።

10. ክፉ ሰው ይህን በማየት ይበሳጫል፤ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፤የክፉዎችም ምኞት ትጠፋለች።

መዝሙር 112