መዝሙር 111:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ።በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።

2. የእግዚአሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።

3. ሥራው ባለ ክብርና ባለ ግርማ ነው፤ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

መዝሙር 111