መዝሙር 107:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

29. ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።

30. ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።

31. እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

32. በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።

መዝሙር 107