መዝሙር 107:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. እርሱ ተናግሮ ዐውሎ ነፋስን አስነሣ፤ነፋሱም ማዕበሉን ከፍ ከፍ አደረገ።

26. ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ፤ከመከራቸውም የተነሣ ሐሞታቸው ፈሰሰ።

27. እንደ ሰከረ ሰው ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ።

28. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

29. ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።

መዝሙር 107