መዝሙር 107:23-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ፤በታላቅም ውሃ ላይ ሥራቸውን አከናወኑ፤

24. የእግዚአብሔርን ሥራ በዚያ አዩ፤ድንቅ አድራጎቱንም በጥልቁ ውስጥ ተመለከቱ።

25. እርሱ ተናግሮ ዐውሎ ነፋስን አስነሣ፤ነፋሱም ማዕበሉን ከፍ ከፍ አደረገ።

26. ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ፤ከመከራቸውም የተነሣ ሐሞታቸው ፈሰሰ።

27. እንደ ሰከረ ሰው ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ።

28. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

29. ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።

30. ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።

31. እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ፣ለሰው ልጆችም ስላደረገው ድንቅ ሥራ ያመስግኑት፤

32. በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።

33. ወንዞችን ወደ ምድረ በዳ፣የውሃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ ምድር ለወጠ።

መዝሙር 107