መዝሙር 107:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤

3. ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ።

4. አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ አጡ።

5. ተራቡ፤ ተጠሙ፤ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።

መዝሙር 107