መዝሙር 107:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።

2. እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤

3. ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ።

4. አንዳንዶቹ ጭው ባለ በረሓ ተቅበዘበዙ፤ወደሚኖሩባት ከተማ የሚያደርስ መንገድ አጡ።

5. ተራቡ፤ ተጠሙ፤ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።

6. በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

መዝሙር 107