መዝሙር 106:34-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት፣ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኋላ አሉ፤

35. እንዲያውም ከሕዝቦቹ ጋር ተደባለቁ፤ልማዳቸውንም ቀሠሙ፤

36. ጣዖቶቻቸውንም አመለኩ፤ይህም ወጥመድ ሆነባቸው።

37. ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንለአጋንንት ሠዉ።

መዝሙር 106