መዝሙር 106:32-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤

33. የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።

34. እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት፣ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኋላ አሉ፤

35. እንዲያውም ከሕዝቦቹ ጋር ተደባለቁ፤ልማዳቸውንም ቀሠሙ፤

36. ጣዖቶቻቸውንም አመለኩ፤ይህም ወጥመድ ሆነባቸው።

መዝሙር 106