መዝሙር 106:18-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. እሳት በጉባኤያቸው መካከል ነደደ፤ነበልባሉም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ።

19. በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።

20. ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣በበሬ ምስል ለወጡ።

21. በግብፅ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤

22. እርሱ ግን በካም ምድር ድንቅ ሥራ፣በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ።

23. ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር።

መዝሙር 106