መዝሙር 105:33-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፤የአገራቸውንም ዛፍ ከተከተ።

34. እርሱ በተናገረ ጊዜ አንበጣ መጣ፤ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ ከተፍ አለ፤

35. የምድሪቱንም ዕፀዋት ሁሉ በላ፤የመሬታቸውንም ፍሬ ሙጥጥ አደረገ፤

36. ደግሞም በአገራቸው ያለውን በኵር ሁሉ፣የኀይላቸውንም ሁሉ በኵራት መታ።

37. የእስራኤልንም ሕዝብ ብርና ወርቅ ጭኖ እንዲወጣ አደረገ፤ከነገዶቻቸውም አንድም አልተደናቀፈም።

38. እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና፣ወጥተው ሲሄዱ ግብፅ ደስ አላት።

39. ደመናን እንደ መጋረጃ ዘረጋላቸው፤እሳትም በሌሊት አበራላቸው።

መዝሙር 105