መዝሙር 105:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ሕዝቡን እንዲጠሉ፣በባሪያዎቹም ላይ እንዲያሤሩ ልባቸውን ለወጠ።

26. ባሪያውን ሙሴን፣የመረጠውንም አሮንን ላከ።

27. እነርሱም ታምራታዊ ምልክቶችን በመካከላቸው፣ድንቅ ነገሮቹንም በካም ምድር አደረጉ።

28. ጨለማን ልኮ ምድሪቱን ጽልመት አለበሰ፤እነርሱም በቃሉ ላይ ማመፅን ተዉ።

29. ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሦቻቸውንም ፈጀ።

መዝሙር 105