መዝሙር 104:7-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ።

8. በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።

9. ተመልሰው ምድርን እንዳይሸፍኑ፣አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው።

10. ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤በተራሮችም መካከል ይፈሳሉ፤

11. የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ።

12. የሰማይ ወፎች ጎጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ።

13. ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች።

14. ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ለእንስሳት ሣርን፣ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤

15. የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።

16. ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤

17. ወፎች ጎጆአቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች።

18. ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።

መዝሙር 104