መዝሙር 104:17-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ወፎች ጎጆአቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች።

18. ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።

19. ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች።

20. ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ።

21. የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ።

22. ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤በየጐሬአቸውም ገብተው ይተኛሉ።

23. ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።

24. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው!ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።

መዝሙር 104